Header Topbar

Sex Strike in America!

Sex Strike in America!
• “The strike will continue until abortion is approved at the federal level.”

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!
Photo credit: Social media

የወሲብ ማቆም አድማ በአሜሪካ !
• “ጽንስ ማስወረድ በፌደራል ደረጃ እስኪፈቀድ አድማው ይቀጥላል”
ታላቋ አገር አሜሪካ፤ ለዘመናት ያኖሯትን መልካም ባህሎችና እሴቶች በአንድ ጀንበር አጠፋፍታ ለመቀመጥ የተጣደፈች ትመስላለች፡፡ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፣ ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የህግ የበላይነት፣ ነጻ ሚዲያ፣ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋችነት፣ ወዘተ– የአሜሪካ በረከቶች ሆነው ለዘመናት ዘልቀዋል፡፡
ዛሬ ግን እኒህ ለዓለም የተረፉ በጎ እሴቶች፣ በፍጥነት እየተሸረሸሩ ነው – ዕድሜ ለግራ ዘመም ዲሞክራቶች፣ ዕድሜ ለጽንፈኛ አክቲቪስቶች!! በስልጡን የፖለቲካ ባህሏና በዲሞክራሲያዊ ሥርዓቷ ዓለም ሲቀናባት የኖረችው አገር፣ ቀኝ ኋላ ዙር የተባለች ትመስላለች፡፡ የእነ ቻይና፣ ሩሲያና ኢራን መሳቂያና መሳለቂያ እስከመሆን ደርሳለች፡፡
የአገሪቱ ትላልቅ ሚዲያዎች ከጋዜጠኝነት ይልቅ በአክቲቪዝም ሥራ መጠመዳቸው እየተነገረ ነው፡፡ በግላጭ የእነ ጆ ባይደን ፓርቲ ልሳን የሆኑም አልጠፉም፡፡ ሃቀኝነት – ሚዛናዊነት – ገለልተኝነት – የሚባሉት የጋዜጠኝነት ሙያዊ መርሆዎች ተረስተዋል፡፡ እነ ሲኤንኤን በኢትዮጵያ የሰሜኑ ጦርነት፣ እንዴት ያለ ወገንተኛ ዘገባ ሲያቀርቡ እንደነበር ታዝበናል፡፡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ፌክ ኒውስ (የፉገራ ዜና እንደማለት) ያሏቸው ከመሬት ተነስተው አይደለም፡፡ እነዚህ የሚዲያ ተቋማት ታዲያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተዓማኒነታቸውን እያጡ መጥተዋል፡፡ ለምሳሌ ሲኤንኤን በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመልካቾቹ ቁጥር ማሽቆልቆሉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በአሜሪካ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ወደፊት በስፋት እንመለስበታለን፡፡ ለአሁን ግን ወደ ሰሞነኛው የአሜሪካ አነጋጋሪ አጀንዳ እንግባ – የወሲብ ማቆም አድማ!!
የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፅንስ ማስወረድ መብትን የተመለከቱ ጉዳዮች በፌደራል መንግስት ሳይሆን በየግዛቱ መንግስታት እንዲወሰኑ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ፣ በውሳኔው የተበሳጩ ጽንፈኛ ዲሞክራቶች፣ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው እንደለመዱት ሲቀውጡት ሰንብተዋል፡፡ ከውሳኔውም በፊት እኒሁ አክቲቪስት ተብዬዎች፣ በዳኞች የግል መኖሪያ ቤት ደጃፍ ላይ ፈጽሞ የማይፈቀድ ተቃውሞ (ማስፈራሪያ ቢባል ይሻላል) ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይሄም ብቻ አይደለም፡፡ በቅርቡ በአንደኛው ጎምቱ ዳኛ ላይ የታቀደ የግድያ ሙከራ በፖሊስ ከሽፏል፡፡
ከዚህ ሁሉ በኋላ ነው የጽንስ ማስወረድ መብት ተሟጋች ነን ባዮች፣ ባለፈው ሳምንት፣ የወሲብ ማቆም አድማ ያሉትን አስገራሚ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ይፋ ያደረጉት፡፡ በአደባባይ ያልተሳካውን ንቅናቄ ወደ ጓዳ አመጡት፡፡ አልጋን የትግል መድረክ አደረጉት፡፡ ይህ የጽንፈኛ አክቲቪስቶች ሃሳብ ነው የተባለ የወሲብ ማቆም አድማ፣ ትዳር ላይ ስለሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ አስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ አድማውን አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለት መሆኑ ነው፡፡ “የጽንስ ማስወረድ መብት በፌደራል ደረጃ እስኪፈቀድ ድረስ አድማው ይቀጥላል!“ ነው ያሉት በደፈናው፡፡ ትግሉ 50 ዓመት ቢፈጅ ብላችሁ አስቡት፡፡ (if ነው እንግዲህ!) ሌላ ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ቀውስ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ (አያድርስ ነው!)
በአሜሪካው ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያ ፎክስ ኒውስ ዘገባ መሰረት፤ አሜሪካውያን አድማውን በተመለከተ የተደበላለቀ ስሜት ነው ያንጸባረቁት፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ብዙዎች የሚቀበሉትና የሚደግፉት እንቅስቃሴ እንደማይሆን ነው፡፡ የሃሳቡ ዋነኛ አቀንቃኞች ግን “መብታችንን የምናስፈጽምበት ትልቁ ሃይል በእጃችን ነው“ ሲሉ ተደምጠዋል – በእልህ ተሞልተው፡፡ (“የፍቅር አጋሮቻችሁን ወሲብ በመንፈግ መብታችሁን አስከብሩ“ የሚሉ ይመስላሉ፡፡)
እኔ ግን ስለዚህ የወሲብ አድማ ሳሰላስል አንድ ዕድሜ-ጠገብ የሃበሻ ተረት ነው ትዝ ያለኝ፤ “ሚስት ባሏን የጎዳች መስሏት —” የሚለው፡፡
አንድ የፎክስ ኒውስ ተንታኝ እንዳለው፤ ይህ የወሲብ ማቆም አድማ አንድ በጎ ጎን አለው፤ ይኸውም በትክክል ከተተገበረ የጽንስ ማስወረድ መብት ውዝግቡን ያስቆመዋል፡፡ እንዴት ከተባለ… የወሲብ ማቆም አድማ ማለት ከእርግዝና ነፃ መሆን ማለት ነው። እርግዝና ከሌለ ደግሞ የጽንስ ማስወረድ ጉዳይ አጀንዳ ወይም ውዝግብ መሆኑ ያከትምለታል። ወሲብ ከሌለ –እርግዝና የለም— እርግዝና ከሌለ ደግሞ—የጽንስ ማስወረድ አያስፈልግም እንደማለት፡፡

ምንጭ: አዲስ ማለዳ

Sex Strike in America!
• “The strike will continue until abortion is approved at the federal level.”
United States of America; She seems to be in a hurry to get rid of the good traditions and values ​​she has kept for centuries. Freedom of expression, democratic political system, rule of law, free media, human rights advocacy, etc. have been a blessing to the United States for centuries.
Today, these values ​​of the world are rapidly eroding – for left-wing Democrats, for extremist activists !! The country, which has been envied by its civilized political culture and democratic system, seems to have turned right. It has become a laughing stock for China, Russia and Iran.
The country’s major media outlets are reportedly more involved in activism than journalism. Apparently, Joe Bidon’s party tongues have not disappeared. The professional principles of journalism, honesty, fairness, and neutrality have been forgotten. We have seen the CNN report biasedly about the war in northern Ethiopia. Former United States President Donald Trump’s Fake News (Fugera News) did not come from the ground up.
These media outlets have become increasingly unreliable. For example, CNN reports that the number of viewers has declined in a short period of time.
We will return to the current political situation in the United States. For now, let’s move on to the current American agenda – sex strike !!
Extremists outraged by the ruling, as the Supreme Court ruled that abortion rights should not be decided by the federal government but by state governments. Prior to the ruling, the so-called activists had been protesting in front of the judges’ private residence. And not only this. A recent assassination attempt on a Gomtu judge has failed.
It is only after this that the so-called abortion advocates announced the shocking protests last week. They brought the failed movement to the chamber. They made the bed a platform for struggle. So far no one was able to send in the perfect solution, which is not strange. What makes the strike worrying is that there is no deadline. “The strike will continue until the right to abortion is granted at the federal level!” Imagine if the struggle lasted 50 years.
(If so!) Another natural and social crisis is likely to occur. (No!)
According to Fox News, a popular American television station: Americans have expressed mixed feelings about the strike. It is safe to say, however, that this is not a movement that many accept. Proponents of her case have been working to make the actual transcript of this statement available online. (They seem to be saying, “Respect your rights by not having sex with your partners.”)
But as I meditate on this sex strike, I remember an old Habesha story; “A wife thinks she has hurt her husband —“
According to a Fox News analyst: This strike has one positive side: Properly covered, it will withstand a great deal of adverse conditions. How to say: A sex strike means to be free from pregnancy. Without pregnancy, abortion is no longer an issue. If there is no sex – there is no pregnancy —
If there is no pregnancy — there is no need for an abortion.

Sex Strike in America!
Spread the love
Scroll to top

You cannot copy content of this page