Header Topbar

የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት አከፋፈል መመሪያ – Higher education cost sharing payment guidelines

የወጪ መጋራት ክፍያ – Cost sharing fee

በሀገራችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተምረው የሚወጡ ዜጎች የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ክፍያ አሰባሰብና አፈጻጸም መመሪያ ማሻሻያ ቁጥር 02/2009 እና የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ደንብ ቁጥር 154/2000 መሰረት ከተመረቁ በኋላ የወጪ መጋራት ክፍያን የሚከፍሉ ሲሆን ቀጥሎ ያለው መረጃ ስለ ስለ አከፋፈሉ ያትታል፡፡
የአከፋፈሉ ሁኔታ
 ተጠቃሚው ከተመረቀ ከአንድ ዓመት በኋላ ጀምሮ ከወር ገቢው በየወሩ ቢያንስ 10 በመቶ እየቀነሰ በመ/ቤቱ በኩል መክፈል አለበት፤
 በግሉ የሚሰራ ተጠቃሚ የሚችለውን ያህል መጠን በክፍለ-ከተማዎች መስተናገድ ይችላል፤
 ማንኛውም ተጠቃሚ ሥራ በሚለቅበት ወቅት የወጪ መጋራት ክፍያ ስለመክፈሉ ወይም ስለማገልገሉ መረጃ መያዝ ይኖርበታል፡፡
የወለድ አከፋፈል
 ተጠቃሚው የሚከፍለው የሚፈለግበትን እዳ ከነወለዱ ነው፡፡ የወለድ አሰላሉ ተጠቃሚው ውለታ በገባበት (በትምህርት ላይ በነበረበት) ወቅት በሀገሪቱ የሚሰራበት የተቀማጭ ወለድ መጠን ይሆናል፡፡ ወለዱ የሚታሰበው ተጠቃሚው ከተመረቀ ከአንድ ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኋላ ነው፤
 ተጠቃሚው ትምህርቱን ሳይጨርስ በማንኛውም ምክንያት ቢያቋርጥም እስካቋረጠበት ጊዜ የሚፈለግበትን ክፍያ ከነወለዱ መክፈል ይኖርበታል፡፡
የዕዳ ስረዛና ተቀናሽ
 ተጠቃሚው በማንኛውም የመንግሥት ት/ቤት በማስተማር ያገለገለ ከሆነ ዕዳው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ይሰረዝለታል፡፡
የክፍያው የጊዜ ገደብ
 ተጠቃሚው ያለበትን ዕዳ ከ15 ዓመታት ባልበለጠ ጊዜ ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
ዕዳን በአገልግሎት መክፈል
 ማንኛውም በጤና ወይም በትምህርት ሙያ የሰለጠነ ተጠቃሚ የወጪ መጋራት ክፍያ ግዴታውን መንግሥት (ጤና ትበቃ ትምህርት ሚኒስቴር) በሚመድበው ቦታ ለሰለጠነበት ጊዜ እኩል አገልግሎት በመስጠት ይወጣል፤
 መንግሥት በመደበው ቦታ አገልግሎት መስጠት ያልቻለ ተጠቃሚ የትምህርቱን ሙሉ ወጪ እና 50 በመቶ ቅጣት ይከፍላል፡፡ አገልግሎቱን ሳይጨርስ ያቋረጠ ተጠቃሚ ያገለገለበት ዘመን ታስቦ ቀሪውን ክፍያ ከነቅጣቱ ይከፍላል፤
 በጤና እና በትምህርት ሙያ የሚሰለጥን ባለሙያ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ በራሱ ጊዜና ፍላጎት ቢያቋርጥ መቀጫው ይመለከተዋል፡፡
የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች
 ተጠቃሚው ከዕዳ ነጻ ደብዳቤ ለመውሰድ ወደ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በሚመጣበት ወቅት፤
 በመስሪያ ቤቱ በኩል ከከፈለ የከፈለውን መጠን እና ሙሉ ስሙን ከነአያት የሚያሳይ ደብዳቤ
 ጊዜያዊ (Temporary) ዲግሪ፤
 ከዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን የወጪ መጋራት ውል፤
 በአገልግሎት ከተወጣ ሙሉ ስሙን ከነአያት እንዲሁም የአገልግሎት ዘመኑን የያዘ ደብዳቤ፤
 በመንግሥት ተመድቦ ካገለገለ መመደቡን የሚገልጽ ማስረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ወይም ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

ምንጭ :- ገቢዎች ሚኒስቴር

የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት አከፋፈል መመሪያ – Higher education cost sharing payment guidelines
Spread the love
Scroll to top

You cannot copy content of this page