በጥናታዊ ጽሁፍ Meta Analysis ምንድን ነው?
Meta-analysis ሌሎች አጥኚዎች መረጃ ሰብስበው ያገኙትን የጥናት ውጤት እርስ በእርስ በማነጻጸር ብቻ በአማካኝ የመጣውን ውጤት መውሰድ የሚቻልበት የጥናት ዘዴ ነው፡፡ Meta-analysis የሚለው ቃል ሲተረጎም analysis of analyses ማለት ነው::
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!ሁላችሁም እንደምታውቁት ጥናታዊ ስራዎችን ለማከናወን በዋናነት ከ Primary source (መጠይቅ በመሰብሰብ (Questionnaire)፤ ቃለ መጠይቅ (Interview) በማድረግ እና የጋራ ውይይት በማካሄድ (Focus Group Discussion) ወይም ከ Secondary source ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በጽሁፍ ያለ ጥሬ መረጃ በማሰባበስ የሚፈለገው ውጤት ላይ መድረስ የተለመደ አሰራር ነው፡፡ Meta-analysis የ Secondary source መረጃ ዘዴ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡
በተቃራኒው ሌሎች አጥኚዎች ከላይ የተዘረዘሩትን መንገዶች ተጠቅመው መረጃ በማሰባሰብ ያገኙትን የጥናት ውጤት (በተመሳሳይ ርዕስ ላይ የተደረገ ጥናት መሆን አለበት) የአንዳቸውን ግኝት ከሌላኛው ግኝት ጋር እርስ በእርስ በማነጻጸር ብቻ በአማካኝ የመጣውን ውጤት መውሰድ የሚቻልበት የጥናት ዘዴ ነው፡፡
በዓለም ላይ የመጀመሪያው የተለያዩ ጥናቶችን በማነጻጸር የተሰራው ጥናት 1904 ነበር (115 ዓመታት አልፎታል)፤ Karl Pearson የተባለ ስታትሽያን በታይፎይድ ላይ የተሰሩ ጥናታዊ ስራዎችን በማሰባሰብ እና ውጤታቸውን በማነጻጸር የማጥናት አካሄድን ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን Meta-analysis የሚለውን ስያሜ በ1976 እንዲያገኝ ያደረገው እና ለጥናቱ ዘዴ ህጎችን በማውጣት በፈጣሪነት የሚጠቀሰው Gene V. Glass የተባለው ስታትሽያን ነው፡፡
የ Meta-analysis ጠንካራ ጎን
👉ለእውነት የተጠጋ ውጤት የማግኘት እድሉ ሰፊ ነው፡፡
👉ብዙ ዳታ የመዳሰስ እድል ይፈጥራል (#ለምሳሌ:- የ300 ሰው መረጃ የወሰዱ 10 ጥናቶችን በ Meta-analysis ዘዴ የሚመለከት አጥኚ በቀላሉ የ3000 ሰዎችን መረጃ እንደሰበሰበ ይቆጠራል)፡፡
👉ናሙና ከመውሰድ የሚመጣን ስህተት (Sampling error) የመቀነስ አቅም አለው፡፡
Meta-analysis ለመጠቀም በመጀመሪያ ለማረጋገጥ በፈለጉት ሃሳብ ዙሪያ የተሰሩ ተቀራራቢ ጥናቶችን በደንብ ማንበብ፤ ጥናቶቹን በርዕሳቸው፤ የተጠቀሙትን Variables እና የተሰሩበት ወቅት መሰረት በማድረግ ማሰባሰብ እና ወደ ማነጻጸሩ መግባት ይጠበቃል፡፡
#ለምሳሌ:- በምስራቅ አፍሪካ ስላለ የስራ አጥነት ምክንያት ለማጥናት የፈለገ አንድ አጥኚ በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መዞር ሳይጠበቅት በምስራቅ አፍሪካ ዙሪያ ባሉ ሀገራት #ለምሳሌ:- ከ2010 እስከ 2019 የተጠኑ የስራ አጥነት ምክንያት የሚሉ የጥናት ስራዎችን ማሰባሰብ ይጀምራል፡ #ለምሳሌ:- በኢትዮጲያ፤ በኤርትራ፤ በጅቡቲ፤ በኬኒያ እና በኡጋንዳ የተሰሩ ሁለት ሁለት ጥናት ቢያሰባስብ በድምሩ አስር የጥናት ግኝት ያገኛል ማለት ነው፡፡
ከዚህ በመነሳት በአብዛኛው ሃገራት የተገኘው ውጤት ሲታይ በአማካኝ አብዛኛዎቹ ያገኙት ውጤት ግብርና ላይ ጥገኛ የሆነ ኢኮኖሚ መኖር ተጨማሪ የስራ እድል ለመፈጠር አለመቻሉን እና ለከፍተኛ ስራ አጥነት ምክንያት መሆኑን ካመላከቱ Meta-analysis የሚጠቀመው አጥኚ ከዚህ አማካኝ ግኝት በመነሳት “በምስራቅ አፍሪካ ላለው ከፍተኛ ስራ አጥነት በቀጠናው ባሉ ሀገራት ግብርና ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት በመሆኑ ነው” ብሎ ያስቀምጣል እንደማለት ነው፡፡
What is Meta Analysis in a research paper?
Meta-analysis is a method by which other researchers can compare the results of a study by comparing them with each other. The term meta-analysis means analysis of analyses.
As you all know, it is a common practice to get the desired results from a Primary source (Questionnaire); Meta-analysis is included in the Secondary source information method.
On the contrary, it is a method of compiling the results of other studies using the methods listed above (should be a study on the same topic) and comparing the results of one study with that of the other.
The first comparative study in the world was made in 1904 (115 years ago); Karl Pearson, a statistician, began researching typhoid and comparing their results. However, it was Gene V. Glass, the inventor of Meta-analysis in 1976, who invented the rules for the method of study.
The strengths of Meta-analysis
👉 The chances of getting close to the truth are high.
Creates the opportunity to explore a lot of data (# For example, a researcher who uses 10 studies of 300 people using a meta-analysis method simply collects data from 3,000 people).
Sampling error can be reduced.
To use Meta-analysis first, read closely the related studies on the idea you want to verify; Topic studies by topic: Collect and compare based on the Variables used and the time of manufacture.
For example, a researcher who wants to study the causes of unemployment in East Africa will not be able to travel to all the countries in East Africa. In Eritrea; In Djibouti: If he collected two studies from Kenya and Uganda, he would get a total of ten studies.
According to Meta-analysis, the results obtained in most countries indicate that the existence of an agricultural-dependent economy does not create more jobs and causes higher unemployment. It is the basis of the economy. ”