የአጭር ጊዜ ሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ ከተመዘገቡት የመራጮች መዝገብ መረጃ ውስጥ በሙከራ ደረጃ ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ሥራ ለማሠራት ባቀደው መሠረት ሥራውን ለማከናወን የሚችሉ ብቃት ያላቸውን ባለሞያዎች መልምሎ ለአጭር ጊዜ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መረጃን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት (Data Encoding) የሥራ ልምድ ያላቸሁ፡-
1. በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ ቢያንስ በድግሪ የተመረቃችሁ
2. ቢያንስ የአንድ ዓመት የሥራ ልምድ (በተለይ በዳታ ማስገባት (Data encoding) ላይ ልምድ ያላቸው ቢሆን ይመረጣል)
3. የሥራ ቋንቋውን አቀላጥፈው ማንበብና መፃፍ የሚችሉ
4. ሴቶች አመልካቾች የሥራ ልምዱ ካላቸውና ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሆነ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
ሥራውን በቅልጥፍና፣ በጥራትና በሥነ ምግባር ማከናወን የምትችሉ አመልካቾች ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ እንድታመለክቱ እየጠየቅን የመጀመሪያውን የምልመላ ደረጃ ያለፉ አመልካቾች በኦንላይንና በአካል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ https://PVLD.nebe-elections.org/form
ማሳሰቢያ፡ ሥራው የሚከናወነው በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ፣ በሶማሊኛ እና በአፋርኛ ቋንቋዎች እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ በመሆኑ አመልካቾች ከአራቱ ቋንቋዎች መካከል በሚገባ መጻፍ ማንበብ እና መረዳት በምትችሉት ቋንቋ እንድታመለከቱ እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
Short term employment notice
The National Election Board of Ethiopia wants to recruit qualified professionals to carry out the work for a short period of time as it plans to enter the voter register data registered in the 6th national election into the database on a trial basis.
Therefore, those who have the experience of entering information into a database (Data Encoding):-
1. Graduated with at least a degree in any field of study
2. At least one year of work experience (especially experienced in data encoding is preferred)
3. Those who can read and write the working language fluently
4. Female applicants will be given priority if they have work experience and meet other requirements.
Applicants who can perform the work efficiently, qualitatively and ethically, please click the button below to apply between October 3rd and October 13th, 2015. APPLY NOW
Note: Since the work is carried out in Amharic, Oromo, Somali and Afar languages and in Addis Ababa city, we inform applicants to apply in the language they can read and write well among the four languages.
Application Deadline: October 23, 2022
National Election Board of Ethiopia
Stay in touches and follows us on our social media platforms to get the latest jobs opportunities.
Join our telegram channel
https://www.t.me/Ethiojob1Vacancy