Header Topbar

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማን ተግባራዊ አደረገ | Addis Ababa city administration rent subsidy for government employees

Addis Ababa City administration

Addis Ababa city administration implemented rent subsidy for government employees.

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

Addis Malala heard that the Addis Ababa city administration is implementing housing rent subsidies, allowances and other benefits for government employees due to the current cost of living.
In order to reduce the cost of living of government employees, the city administration cabinet passed a resolution on August 27/2014 to increase the rent subsidy, professional job responsibility allowance, mobile card and transportation allowance.
It was also pointed out in the execution document that the rent allowance subsidy is intended to alleviate the problem that has been repeatedly complained about for many years due to the constant increase in rent due to the housing problem of the city administration.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማን ተግባራዊ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለው ወቅታዊ የኑሮ ውድነት ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማ አበል እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።

የመንግሥት ሠራተኞች የሚያነሱትን የኑሮ ውድነት ለማቃለል እንዲቻል የቤት ኪራይ ድጎማ፣ ሙያዊ የሥራ ኃላፊነት አበል፣ የሞባይል ካርድና የትራንስፖርት አበል ጭማሪ እንዲደረግ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ነሐሴ 27/2014 የውሳኔ ሐሳብ ማሳለፉን አዲስ ማለዳ ውሳኔው ተግባራዊ እንዲደረግ ለክፍለ ከተሞች ከተላለፈው ማስፈጸሚያ እንደተመለከተች አሳውቃለች።
የቤት ኪራይ አበል ድጎማውም በአሁኑ ሰዓት በከተማ አስተዳደሩ ካለው የቤት ችግር አንጻር የቤት ኪራይ በየጊዜው በመጨመሩም የመንግሥት ሠራተኞች በከፍተኛ ደረጃ ተጎጂ በመሆናቸውና ለረጅም ዓመታት ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረውን ችግር በተወሰነ መልኩ ለማቃለል ታሳቢ የተደረገ መሆኑም በማስፈጸሚያ ሰነዱ ላይ ተመላክቷል።

አዲስ ማለዳ የተመለከተችው የማስፈጸሚያ ሰነድ እንደሚያስረዳው፣ የቤት ኪራይ ድጎማና አበል ክፍያ ቀደም ሲል የተፈቀደላቸው የሥራ መደቦች ላይ የተመደቡ ማለትም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲኖችና አሠልጣኞች፣ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራን እና መምህራን፣ አቃቤ ሕግ ባለሙያዎች፣ የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች ዳኞች እና የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ዳኞችን አያካትትም የሚል ነው።

የኃላፊነት አበል ክፍያ ተፈጻሚ የሚሆነውም በሆስፒታል እና ጤና ጣቢያዎች በሥራ ኃላፊነት ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች ነው። ሰነዱ አክሎም የትራንስፖርት አበል ተፈጻሚ የሚሆነው በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በሆስፒታልና ጤና ጣቢያ ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ላይ ነው። የሞባይል ስልክ ክፍያ አበል ተፈጻሚ የሚሆነው በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ ከቡድን መሪ ጀምሮ በተመደቡት እና በአማካሪ ደረጃ መሆኑን መረጃው ያትታል።
አዲስ ማለዳ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኛ ከሆኑ ሰዎች እንደሰማችው፣ ደሞዛቸው ከ4 ሺሕ ብር በታች ለሆነ ሠራተኞች የቤት ኪራይ 1 ሺሕ 500 ብር ጭማሬ ተደርጓል ሲል በድረገጹ አስነብቧል። በውኔው መሠረት እርሳቸው የሐምሌና የነሐሴ ወር ክፍያ መስከረም ወር ላይ እንደተፈጸመላቸው ጠቅሰዋል ሲል ገልጿል።

ደሞዛቸው ከ4 ሺሕ ብር በላይ ለሆነ ሠራተኞችም ከተደረገው የቤት ኪራይ ድጎማ በተጨማሪ፣ ለጽዳትና የጥበቃ ሠራተኞች እንደየሁኔታው የወተት አበል ተብሎ ተጨማሪ ብር ያገኛሉ።
የተፈቀደው ጥቅማ ጥቅም በከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እውቅና የተቀጠሩ የኮንትራት ቅጥር ሠራተኞችንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል።

በዓመት ፈቃድ፣ በወሊድ ፈቃድ፣ በሀዘን ፈቃድ፣ በሕመም ፈቃድ፣ በረዥም ጊዜ ትምህርትና በአጭር ጊዜ ሥልጠና ከመደበኛ ሥራ ውጭ ለሆነ ሠራተኛ የቤት ኪራይ ድጎማ አበል ክፍያ የሚፈጸም ሲሆን፣ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ከ30 ቀናት በላይ ከመደበኛ ሥራ ውጪ ለሆነ ሠራተኛ የኃላፊነት አበል፣ የስልክ ክፍያ አበል እንዲሁም የትራንስፖርት አበል ክፍያ መፈጸም የተከለከለ ነው ተብሏል ሲል ገልጿል።

የተፈቀደው የቤት ኪራይ ድጎማ አበል እና የጥቅማ ጥቅም አበል ክፍያ ከሥራ ግብር ነጻ ነው።
ምንጭ:- አዲስ ማለዳ

N.B: Sewaseweth.com website is an online jobs search engine for jobs seekers in Ethiopia and other countries. If you are looking latest jobs in Ethiopia and other contents you are in the right place. In addition to this, we offer you new international scholarship opportunities. Just remember to visit the official website for the latest jobs vacancy. You can access new job vacancies easily where you are.
ድረ-ገጽ:- www.sewaseweth.com
Stay in touches and follows us on our social media platforms to get the latest jobs opportunities.
Join our telegram channel
https://www.t.me/Ethiojob1Vacancy

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች የቤት ኪራይ ድጎማን ተግባራዊ አደረገ | Addis Ababa city administration rent subsidy for government employees
Spread the love
Scroll to top

You cannot copy content of this page