የግል መገልገያ ዕቃዎች ወደአገር የሚገቡበትን ሁኔታ የሚወስነው በሥራ ላይ ያለው መመሪያ ለሕገ ወጥ ንግድ በር የከፈተ እና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ዓለምአቀፍ አሠራሮችን በተከተለ አኳኋን መመሪያውን አሻሽሎ ማውጣት በማስፈለጉ፤
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!The current directive that determines the conditions for the entry of personal appliances into the country has opened the door to illegal trade and has had a negative impact on the provision of services.
በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (በአዋጅ ቁጥር 1160/2011 እንደተሻሻለው) አንቀፅ 33(2) የግል መገልገያ ዕቃዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው ወደ አገር የሚገቡበት እና ከአገር የሚወጡበትን ሁኔታ እንዲወስን ለገንዘብ ሚኒስቴር ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ፤
የገንዘብ ሚኒስቴር የሚከተለውን መመሪያ አውጥቷል፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌ
ከፍል አንድ
1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ ‘ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ አገር የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ ዕቃዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 923/2014” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
- ትርጉም
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፣
1) ”ለንግድ የማይውል ዕቃ” ማለት ጠትላላ ብዛቱ በዚህ መመሪያ ከተወሰነው መጠን ያልበለጠ፤ ለባለመብቱ ወይም ለቤተሰቡ የግል መገልገያ ወይም ፍጆታ የሚውል ባለመብቱ ይዞት ወይም ከባለመብቱ ተለይቶ የሚመጣ ዕቃ ነው።
2) ”ለንግድ የማይውል ዕቃ” ማለት ጠቅላላ ብዛቱ መጠን በዚህ መመሪያ ከተወሰነው የማይበልጥ፤ ለባለመብቱ ወይም ለቤተሰቡ የግል መገልገያ ወይም ፍጆታ የሚውል ባለመብቱ ይዞት ወይም ከባለመብቱ ተለይቶ ወደ አገር የሚገባ ወይም ከአገር የሚወጣ ዕቃ ነው።
የመመሪያውን ሙሉ ሰነድ በPDF ከታች ማግኘት ትችላላችሁ።
Directive No. 923 – 2014 issued to determine goods imported or exported for personal use
ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ አገር የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ ዕቃዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 923 – 2014