የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ
.
በዛሬዉ ዕለት 14ኛዉ ዙር የ20/80 እና 3ኛ ዙር 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት በአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር ለባለእድለኞች ወጥቷል።
በዚህም 20/80 ነባር ተመዝጋቢዎች የ18 ሺሕ 630 ቤቶች ዕጣ፣ የ20/80 አዲስ ተመዝጋቢዎች ዕጣ ከ318 ቤቶች ውስጥ የ300 ተመዝጋቢዎች ዕጣ እንዲሁም የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች የ6 ሺሕ 834 ቤቶች ዕጣ ወጥቷል።
የ20/80 አዲስ ተመዝጋቢዎች ዕጣ 18 የስቱዲዮ ቤቶች ሆነው ቆጣቢ የሌላቸው መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ለጊዜው ቤቶቹ ለማንም በዕጣ እንደማይተላለፉ ተነግሯል።
በዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ ላይም የመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ፣ ሴቶች 30 በመቶ፣ አካል ጉዳተኞች 5 በመቶ እንዲሁም ቀሪው 45 በመቶ በእጣ ባለእድለኞች እንደተለዩ ተገልጿል።
በተጨማሪም በባለሶስት መኝታ 300 መቶ ቤቶችን ቀሪ ሥራ በማከናወን ለነባርና አዲሰ ተመዝጋበዎች በዕጣ መካተታቸው ተነግሯል።
በዚህ ዕጣ የ20/80 ከ96 በመቶ በላይ፣ በ40/60 ከ87 በመቶ በላይ የግንባታ አፈጻጸም ያላቸው ቤቶችን ለዕጣ መቅረባቸውም ተገልጿል፡፡
አጠቃላይ 20-80 አዲስ የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ስም ዝርዝር
20_80 New Housing programme winners name list
አጠቃላይ 40-60 የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ስም ዝርዝር
አጠቃላይ 20-80 ነባር የቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ስም ዝርዝር
የመረጃው ምንጭ: የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት