የደም ግፊት ምንድነው እና እንዴት ነው የሚለካው?
የደም ግፊት ምንድ ነው?
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!የደም ግፊት ከልብ ምት የሚመነጭ እና ደም በሰውነት እንዲዘዋወር የሚረዳ የግፊት ሀይል ነው። የደም ግፊት ከሚገባው በላይ ሲጨምር የደም ቧምቧዎችን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። ይህም የደም ግፊት (hypertension ወይም high blood pressure) ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት ይባላል።
ከፍተኛ የደም ግፊትን በሁለት ምድቦች መመደብ ይቻላል።
- ከሌሎች በሽታዎች ወይም መድሀኒቶች ጋር ተያይዞ የሚመጣ ከፍተኛ የደም ግፊ (Secondary Hypertension)
ከአጠቃላይ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመምተኞች አምስት በመቶ የሚሆኑ ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች በዚህ ምድብ ውስጥ ይመደባሉ(Charles, 2017)። የደም ግፊታቸውን ከፍ የሚያደርገው በሽታ ሲድን ወይም መድሀኒቱ ሲቋረጥ የደም ግፊታቸው ሊስተካከል ይችላል፡፡ - መሰረታዊ ከፍተኛ የደም ግፊት (Primary Hypertension)
አብዛኛዎቹ (ከዘጠና እስከ ዘጠና አምስት በመቶ) የሚሆኑ የከፍተኛ ይደም ግፊት ህመምተኞች በዚህ አይነት ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ይጠቃለላሉ(Charles, 2017)። የደም ግፊታቸው ከሌላ ህመም ጋር ሳይያያዝ ወይም ይህ ነው በማይባል ምክንያት ከፍ ይላል። እንዲህ አይነት የደም ግፊት መሰረታዊ ወይም ፕራይመሪ ሀይፐርቴንሽን ይባላል።
የመሰረታዊ ከፍተኛ የደም ግፊት ትክክለኛ መንስኤ አይታወቅም። ነገር ግን የሚከተሉት በዚህ ህመም የመያዝ እድልን ሊጨምሩ ይችላሉ።
• በዘር ከፍተኛ ደም ግፊት መኖር
• ከፍተኛ የጨው መጠን በምግብ ላይ መጠቀም
• ትንባሆ
• አልኮል
• በእድሜ መግፋት
• የኩላሊት በሽታ
• ከልክ ያለፈ ውፍረት
• የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
እንዴት ነው የሚለካው?
የደም ግፊት የሚለካው በሜርኩሪ ሚሊሜትር (ሚሜ ኤችጂ) ነው። የደም ግፊት መለኪያ ሁለት ቁጥሮች አሉት፡- የላይኛው ቁጥር (ሲስቶሊክ) የልብ ጡንቻ ሲጨመቅ (ኮንትራት)፣ ደም በማፍሰስ የደም ፍሰት ግፊት ነው። የታችኛው ቁጥር (ዲያስቶሊክ) በልብ ምቶች መካከል የሚለካው ግፊት ነው.
የከፍተኛ የደም ግፊት (Hypertension) ህመም ምልክቶች
የደም ግፊት በአብዛኛው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ሊሰማቸው ይችላል
• የራስ ምታት
• የአይን ብዥታ
• ራስ ማዞር
• ደረት ላይ የሚሰማ ህመም
የደም ግፊት ለብዙ አመታት ምንም ምልክት ሳያሳይ ህመምተኛውን ሊጎዳ ይችላል። በዚህ ምክንያት አንዳንዴ የደም ግፊት ዝምተኛው ገዳይ በሚል ስም ይጠራል። የደም ግፊት ያለበት ሰው ምልክት ባያሳይም ሰውነቱ እየተጎዳ አይደለም ማለት አይደለም። እንዲያውም ህክምና ያልተደረገለት የደም ግፊት ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል። ከነዚህም መካከል የኩላሊት በሽታ፣ የአይን ህመም እና የልብ እና የደምስር በሽታዎችን ሊያስከትል ይችላል፡፡
ከፍተኛ የደም ግፊትን ለማስተካከል የሚረዱ ዋና ዋና ነገሮች የሚከተሉት ናቸው
• ምግብ ውስጥ የሚጨምሩትን የጨው መጠን መቀነስ
• ጤናማ የሆነ አመጋገብ መመገብ
• የአካል እንቅስቃሴ ማዘውተር
• ውፍረት መቀነስ
• አልኮል መቀነስ
• ሲጃራ አለማጨስ (ትንባሆ በምንም አይነት መልኩ ቢሆን አይጠቀሙ)
• የሀኪም ቤት ቀጠሮ እና ሀኪምዎ የሚያዝልዎትን መድሃኒት ይከታተሉ
• በየጊዜዉ የደም ግፊትወን ቸክ ያድርጉ
What is blood pressure and how is it measured?
What is blood pressure?
Blood pressure is the force exerted by the heartbeat that helps blood move through the body. High blood pressure can damage blood vessels and other parts of the body. This is called hypertension or high blood pressure.
High blood pressure can be classified into two categories.
- High blood pressure associated with other diseases or drugs (Secondary Hypertension)
Five percent of all hypertensive patients fall into this category (Charles, 2017). When the disease causing the high blood pressure is cured or the medication is discontinued, their blood pressure may be normalized. - Primary Hypertension
Most (ninety to ninety-five percent) of hypertensive patients have this type of hypertension (Charles, 2017). Their blood pressure is elevated without any other illness or cause. This type of blood pressure is called basic or primary hypertension.
The exact cause of essential hypertension is unknown. However, the following may increase the risk of developing this disease.
• Living with high blood pressure
• Use of high amount of salt in food
• Tobacco
• Alcohol
• In old age
• Kidney disease
• Excessive obesity
• Inactivity
How is it measured?
Pulse is estimated in millimeters of mercury (mm Hg). A pulse estimation has two numbers: The top number (systolic) is the tension of the blood stream when the heart muscle presses (contracts), siphoning blood. The base number (diastolic) is the strain estimated between pulses.
The clinical term for high blood pressure will be hypertension. In grown-ups, pulse is viewed as ordinary under a systolic worth of 140 mmHg and under a diastolic worth of 90 mmHg.
What is Normal blood pressure?
An ordinary circulatory strain(blood pressure) level is under 120/80 mmHg. Regardless of your age, you can make strides every day to keep your circulatory strain(blood pressure) in a healthy range.
Symptoms of high blood pressure (Hypertension).
High blood pressure can usually be asymptomatic. However, some people may feel the following symptoms
• Headache
• Blurred vision
• Dizziness
• Chest pain
High blood pressure can affect a patient for many years without showing any symptoms. Because of this, high blood pressure is sometimes called the silent killer. Even if a person with high blood pressure does not show symptoms, it does not mean that the body is not being affected. In fact, untreated high blood pressure can lead to various health problems. Among these, it can cause kidney disease, eye disease, and cardiovascular disease.
Following are the main things that help to correct high blood pressure
• Reducing the amount of salt added to food
• Eating a healthy diet
• Exercise routine
• Reduce obesity
• Reduce alcohol
• Do not smoke cigars (do not use tobacco in any form).
• Follow the doctor’s appointment and the medicine that your doctor prescribes
• Check your blood pressure regularly