Header Topbar

COMMON JOB INTERVIEW QUESTIONS – በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ወደ 30 የሚደርሱ ጥያቄዎችንና ልትሰጡ የሚገባቸው ምላሾች

Interview questions

በተደጋጋሚ በስራ ቃለመጠይቅ/ ኢንተርቪው ጊዜ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ወደ 30 የሚደርሱ ጥያቄዎችንና ልትሰጡ የሚገባቸውን ምላሾች እንዲሁም ማድረግ የሚገባችሁን ጥንቃቄ በተመለከተ ለዛሬ 10 ያህሉን ይዘናል ቀሪዎቹን በሌላ ጊዜ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

1,  እስኪ ስለራስህ ንገረን?

ይህ ጥያቄ እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ ቀላል ይመስላል ይሁን እንጂ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት ነው፡፡ ብዙ ተጠያቂዎች ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚመስላቸው ስለራሳቸው የህይወት ታሪክ ማውራት ነው ፡ ይሁን እንጂ እንዲያ ለማለት ሳይሆን በስራ ህይወት ላይ ስላለህ ማንነት ፡ የስራ ልምድ ካለህ በዚያኛው የስራ ቦታ ስላስመዘገብካቸውና ስለሰራሀቸው ጥሩ ስራዎች እንዲሁም ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆንክ በዩኒቨርሲቲ ቆይታህ ስለነበረህ መልካም እንቅስቃሴ ወይም ስለሰራኸው የመመረቂያ ፕሮጀክት ልታወራ ትችላለህ፡፡ በንግግርህም ወቅት ጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንድትሆን ጠቃሚ ነገሮቹ ላይ ትኩረት አድርግ፡፡

2, ስለዚህ የስራ መደብ እንዴት ሰማህ??

ሌላው በተደጋጋሚ የሚጠየቀው ጥያቄ ይሄ ነው ፡ በዚህ ወቅት ማድረግ የሚገባችሁ ነገር በትክክል ስለዚህ የስራ መደብ የሰማችሁበትን ቦታ በግልፅ ተናገሩ ፡ በጋዜጣ ; በማስታወቂያ ቦርድ ; በጓደኛችሁ አልያም በማህበራዊ ድህረ ገፆች ላይ አይቼ አመለከትኩኝ ማለት ትችላላችሁ፡፡

3፡ ስለመስሪያ ቤታችን ምንተውቃለህ?

ይህ ጥያቄ ለጠያቂው የሚሰጠው ትልቅ መልዕክት አለ ፡ በተቻለ መጠን ወዳመለከታችሁበት መስሪያቤት ከመሄዳችሁ በፊት ስለ መስሪያቤቱ በቂ ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል ፡ ተልዕኮውን, አላማውን, ራዕዩን በግልፅ ልትረዱ ይገባል እናንተም በዚሁ መስሪያቤት ተልዕኮ አላማና ራዕይ ውስጥ ልታበረክቱ ስለምትችሉት ነገር በአጭሩ ተናገሩ፡፡

ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት ድህረገጽ ካለው About የሚለውን በመጫን መረጃውን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ አልያም በአንዳንዶቹ ዘንድ ገና ወደ ግቢያቸው ስትገቡ ተገቢውን መረጃ በሆነ ቦርድ ወይም በአንዳች ነገር በግልፅ ተፅፎ ታገኙታላችሁ፡፡

ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለስራው የሰጣችሁትን ትኩረት ያሳያል፡፡

4፡ ለምን እዚህ መቀጠር ፈለክ ?

ብዙውን ግዜ ቀጣሪዎች በቅጥር ወቅት ሊቀጥሩ የሚፈልጉት በተቻለ መጠን ልህቀቱ ጥሩ የሆነውን ሰው ነው እናም ለሚጠየቀው ጥያቄ አሳማኝ መልስ መስጠት አንዱ ማሳያ ነው፡

★የእናንተ መስሪያ ቤት ትኩረት አድርጎ በሚሰራባቸው ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ፡፡

★ መስሪያ ቤቱ ትልቅ እና መልካም እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የዚህ አካል መሆንን ስለምፈልግ፡፡

★ ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመለየት እንደዚያ አይነት ግልጋሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን በህይወታችሁም ላይ እንዲሁም ለህሊናችሁ የሚሰጠውን እርካታ ተናገሩ፡፡

5, ለምን አንተን እንቀጥርሀለን?

እንዲህ የሚል ጥያቄ ከተጠየቃችሁ አልፈለጉኝም ማለት ነው ብላችሁ እንዳትደነግጡ ይልቁን ደስ ሊላችሁ ይገባል ምክንያቱም በጠያቂው ዘንድ ጥሩ ቦታን አግኝታችኃል ማለት ነው ፡ እናም በዚህ ወቅት

★ እናንተን በመቅጠራቸው በመስሪያ ቤቱ ጉዞ ላይ የእናንተን አቅም በመጨመር ተገቢውን አገልግሎት እንደምትሰጡ፡፡

★ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድኑን አንድነት በማጠናከር ለመስሪያቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ ተናገሩ፡፡ እንዲሁም መሰል ምላሾችን አክሉበት

6፡ በሙያህ ጠንካራ ጎኖች አሉኝ ብለህ የምታምናቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

★ ያሉህን እውነተኛ ጥንካሬዎች ተናገር ፡ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ሳይሆን ያለህን ነገር፡፡

★ ከምትወዳደርበት የስራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሙያዊ ጥንካሬዎችን አስቀድም፡፡

7፡ ድክመቶችህ ምን ምን ናቸው?

ሀለሉም ሰው ድክመቶች ቢኖሩበትም ቅሉ በስራ ቃለ መጠይቅ ወቅት እኒህ እኒህ ድክመቶች አሉብኝ ብሎ መናገር አይመከርም ይልቁን የሚታይ ድክመት አለብኝ ብዬ አላምንም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነኝ እኔ ባለብኝ ድክመት ምክንያት ነገሮች ተበላሽተውበኝ አለማወቃቸው አንዱ ማሳያዬ ነው ብሎ መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡

8፡ በሙያህ ያስመዘገብከው ስኬት ምንድነው?

አሁን ልትቀጠርበት ባለው የሙያ ዘርፍ ቀደም ብለህ ያስመዘገብከውን ውጤት ተናገር ፡ የሰራኸውን ነገር መናገር ጉራ አይደለምና ዘና ብለህ ስላበረከትከው ነገር አውራ ፡ ጀማሪ ተቀጣሪም ከሆነክ መመረቂያህ ተግባራዊ ተደርጎ ተሰርቶ ከሆነ እሱን ጥቀስ፡፡

9፡ ቀደም ብሎ በነበረህ የስራ ወቅት የገጠመህ ግጭት ወይም አለመግባባት ነበር ወይ? ከገጠመህስ እንዴት ፈታኸው?

አስተውል ጠያቂህ ይህን ጥያቄ የጠየቀህ ስለአንተ ጀብድ ወይም ሌላ ለመስማት ሳይሆን፡ ለችግሮች ምላሽ የምትሰጥበትን መንገድ ለማወቅ ነው ፡ እናም ጉዳዩ ገጥሞህ ከሆነ የፈታህበትን መንገድ ጥበብ በተሞላበት መልኩ መልስ፡፡

10: ከአምስት አመት በኃላ እደርስበታለሁ ብለህ የምታስበው ራዕይ ምንድነው?

የምር ራዕያችሁ የሆነውን ነገር መናገር ተገቢ ነው ፡ ልትደርሱበት የምትፈልጉበትን ቦታ ግልፅ መሆኑን ሊለካ እና ሊደረስበት የሚችል ነገር ተናገሩ ፡ በዛው መስሪያ ቤት እስከ መጪዎቹ አምስት አመታት የመቆየት ሀሳብ ካላችሁ በዛ መስሪያቤት የት ቦታመድረስ እንደምትፈልጉ ጭምር ተናገሩ፡

ይህም ከእነርሱ ጋር የረጅም ጊዜ እቅድን አንግባችሁ እንደመጣችሁ እንዲረዱ ያደርጋቸዋል፡ እናም ከሌሎች ተወዳዳሪዎች በተሻለ ትኩረት እንድትስቡ ያደርጋችኃል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ እነኚህንና የመሳሰሉትን ነገሮች ተግባራዊ ማድረግ በቃለመጠይቅ ወቅት የተሻለ ማንነት እንድትላበሱ ያደርጋችኃል ብለን እናስባለን፡፡

ክፍል ሁለት እንሆ!!

➊ 11; ለምን አሁን ያለህበትን ስራ ትለቃለህ?

አስተውሉ ለዚህ ጥያቄ በምትመልሱት መልስ ለቀጣሪዎቻችሁ ከአንድ በላይ ትርጓሜን ያሰጣል በመጀመሪያ ደረጃ ቀድሞ ስትሰሩበት የነበረውን መስሪያ ቤት መጥፎነት ለመናገር አትድፈሩ ይልቁን አዲስ ነገር ለማወቅ ፍላጎት እንዳላችሁ ፣ አሁን እየተወዳደራችሁ እንዳላችሁበት አይነት የስራ ዘርፍ ላይ መስራት ህልማችሁ እንደሆነ ፣ ለምሳሌ፦ ያመለከታችሁበት መስሪያ ቤት ለህዝብ አገልገሎት መስጠት ከሆነ ፡ እናንተ በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያገናኙ ስራዎች ላይ መስራት እንደምትፈልጉ ይሁን እንጂ ቀድሞ የነበራችሁበት እንዲህ አይነቱን አገለግሎት እንደማይሰጥ ፡ ከዚህም መነሾነት የቀደመውን ስራችሁን ለመተው እንደወሰናችሁ ተናገሩ፡፡

➋ 12 ፦ ምን አይነት የስራ አካባቢ ያስደስትሀል / የስራ መንፈስ / Work environment ?

በዚህ መስሪያ ቤት ከማመልከታችሁ በፊት በዛ ቦታ ስላለው የስራ መንፈስ በቂ ጥናት እንዳደረጋችሁና እንደተማረካችሁበት በመጥቀስ አሁን እያመለከታችሁ እንዳላችሁበት አይነት የስራ መንፈስን እንደምትመርጡ መናገር ትችላላችሁ፡፡

➌ 13 ፦ ምን አይነት የአመራር ስልትን ትከተላለህ?

ምናልባት አሁን እያመለከታችሁ ያላችሁበት የስራ መደብ የአመራርነት ላይሆን ይችላል ነገር ግን ቀጣሪዎቻችሁ ይህን ጥያቄ የሚጠይቋችሁ ከእነርሱ ጋር በምትዘልቁበት ወቅት ምናልባት በአመራርነት የመስራታችሁ እድል ስላለ ምን አይነት መሪ እንደሆናቸህ ቀድመው የሚለኩበት ነው፡ ጥሩ መሪ ጠንካራ እና ከነገሮች ጋር ተጣጣፊ መሆን የሚችል ፣ በቡድን ስራ የሚያምን እና የገዢነት ሳይሆን የመሪነት ስሜት የሚሰማው አይነት ነው፡፡ እናንተም በእንዲህ አይነት የመሪነት ዘርፍ ውስጥ የምትመደቡ መሆኑን ግለፁ፡፡

➍ 14 ፦ ጓደኞችህ ወይም የቀድሞ አለቃህ ስለአንተ ምን

ይላሉ?

ይህን ጥያቄ ስትመልሱ ታማኝ ሆናችሁ መልሱ ምክንያቱም ሁሉን መስፈርት አሟልታችሁ ለቅጥር ብቁ ከሆናችሁ ወደቀድሞ አለቃችሁ ወይም በCV ላይ ወደገለፃችሁት ሰው መደወላቸው ስለማይቀር፡፡ እውነተኛ ጠንካራ ጎናችሁን በተሰጣችሁ ፕሮጀክት ላይ እስከምን ድረስ ገፍታችሁ እንደምትሄዱ ተናገሩ፡፡

➎ 15 ፦ ለምን ይህን ያክል ጊዜ ሳትቀጠር ተቀመጥክ?

ከተመረቃችሁ በኃላ ወይም ከቀድሞ ስራችሁ ከወጣችሁ በኃላ እስከአሁን ድረስ ( የጊዜ ክፍተት ካለ) ለምን ስራ እንዳልገባችሁና በዚህ ጊዜ ምን ስታደርጉ እንደነበረ ስትናገሩ በተቻለ መጠን ጊዜውን እንዳባከናችሁ አርጎ እንደማይሰማችሁ እና በበጎ ፈቃደኝነትም ይሁን በሌላ መልክ ስታገለግሉ እንደነበረ አልያም ጥቂት ጊዜ እረፍት ማድረግ ፈልጋችሁ እንደነበረ ግለፁ፡፡

➏ 16 ፦ በተቀጠርክ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ምን ትጠብቃለህ?

በተለየ መልኩ የቀጣሪዎችን ትኩረት ለማግኘት ብላችሁ የማይጨበጠና የማይመስል ነገር አትናገሩ፡ መስሪያ ቤቱን መላመድና በአግባቡ ከስራ ባልደረቦቻችሁ ጋር የቡድን መንፈስን በማምጣት ይህንና ያንን ላበረክት እፈልጋለሁ ማለት ይቻላል፡፡

➐ 17 ፦ ስለ ደመወዝ የምትለው ነገር ምንድነው?

ቅጥሩ ሲወጣ ደመወዝ የተገለፀ ወይም በድርጅቱ ስኬል ከሆነ ይህ ጥያቄ አይነሳም ይሁን እንጂ የደመወዝ ሁኔታ በስምምነት ከሆነ እናንተ ሊከፈላችሁ የሚገባውን ደመወዝ ቀድሞ ያሉ ሰራተኞች ከሚከፈላቸውና እናንተ ካለችሁ የትምህርት ዝግጅት ብሎም የስራ ልምድ አንፃር ይህን ያክል ብላችሁ መደራደር ትችላላችሁ ፡ በርግጥ ቀጣሪዎች ይህን ያክል ልንከፍልህ እንችላለን ሊሏችሁ ይችላሉ ነገር ግን እናንተ ሊከፈላችሁ ይገባኛል ከምትሉት ጋር መደራደር ይቻላል፡፡

➑ 18 ፦ ከስራ ውጪ ምን ማድረግ ያስደስትሀል?

ከስራ ውጪ ብዙጊዜ የምታደርጉትን እውነተኛውን ነገር ተናገሩ ምንም እንኳ አንዳንድ ጊዜ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅቡልነት የሌላቸውንና በይፋ የማይነገሩ ባህሪያት ካሏችሁ እነሱን መጥቀስ የእስካሁኑን ጉዞ ውሀ እንዲበላው ሊያስደርግ ስለሚችል ጥንቃቄ አድርጉ፡፡

➒ 19 ፦ እንሰሳ ብትሆን ኖሮ ምን አይነቱን ትመርጥ ነበር?

እንደዚህ አይነት ወጣ ያለ ጥያቄ ለነገሮች ከተለመደው እይታ ውጪ የምትመለከቱበትን መነፅር ለማየት እንጂ ውሻ ወይ ድመት ወይ ደግሞ አንበሳ የሚለውን ለመስማት አይደለም ነገር ግን ለምን ያንን እንደመረጣችሁ የምታስረዱበትን መንገድ ስለሚመዘን ለምትሰጡት መልስ ምክንያታዊ ሁኑ፡፡

➓ 20 ፦ ጥያቄዎች አሉህ?

የመጨረሻው የሚሆነው ጥያቄ የሆኑባችሁን ነገሮች መጠየቅ ነው ስለሆነም እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቃችሁ አመስግኖ መውጣት ነው፡፡

❖ በመጨረሻም ❖

በCV ላይ የፃፋችኃቸው ነገሮችን በአግባቡ ማስተዋል ተገቢ ነው ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ እዛ ላይ ያሉ ነገሮችን ደግመው ስለሚጠይቋችሁ አንድ አይነት ነገር መመለስ መቻል አለባችሁ፡፡

How to write CV

በቀጣሪዎች ዘንድ ተመራጭ CV እንዴት መፃፍ ይቻላል፡፡

CV ማለት የአንድ ሰው የትምህርትና ሌሎች professional ታሪኮቹን በአጭር መልኩ የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡ ብዙ ግዜ ለስራ ማመልከቻነት እንጠቀምበታለን የራሳችንንም ማንነት በጥሩና ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ ያስችለናል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት እንዲቀጥሩን ለምንፈልጋቸው ቀጣሪዎች አሰልቺ ያልሆነና ሳቢ የሆነ CV መፃፍ ትልቅ ትኩረት ለማግኘት ያስችለናል፡፡ ታዲያ እንዴት እንዲህ ያለውን CV መፃፍ እንችላለን እና ምን ምን መካተት አለበት የሚለውን እንመልከት፡፡

፩ ከቀድሞ ስራ ጋር የተያያዙ የስራ ልምዶች፡፡

፪ የትምህርት ሁኔታ እና ሌሎች ተዛማጅ ችሎታዎች

፫ አፃፃፋችሁን ለማንበብ እና ለመረዳት ቀለል ባለመልኩ ይሁን

፬ የስራ ልምድ ካላችሁ በቀደመው ስራችሁ ያሳካችኋቸውን ነገሮች ጥቀሱ፡፡ ጀማሪ ከሆናችሁ ደግሞ በነፃ አገልግሎት እንዲሁም በተማራችሁበት የትምህርት ተቋም ስታደርጉ የነበረውን መልካም እንቅስቃሴ ጥቀሱ፡፡

፭ ፊደላት እና ቃላት አጠቃቀም ትኩረት ማድረግ ፡፡

፮ እናንተ በመስሪያ ቤቱ ብትቀጠሩ ልታበረክቱ የምትፈልጉትንና እናንተ በመቀጠራችሁ በመስሪያ ቤቱ ስኬት ላይ ልትጨምሩ የምትፈልጉትን ጥቀሱ

፯ አድራሻችሁን ስትጠቅሱ የተለያዩ አማራጮችን አስቀምጡ፡ ስልክ ኢሜይል፡፡

፰ ሪፈረንስ ስትጠቅሱ ስለእናንተ በደንብ ሊገልፅ የሚችል ሰው ይሁን፡፡

፱ ከሁለት ገፅ ባይበልጥ መልካም ነው አሰለቺ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፡፡

★★★ማድረግ የሌለባችሁ★★★

1: የቃላትና ፊደላት ግድፈት እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡

2: የማይሰራና የማትገኙበትን አድራሻ አትጠቀሙ፡፡

3: ራሳችሁን ስትገልፁ ግልፅ ያልሆነና የሚያሻማ እንዳይሆን

4: ውሸት!!! ውሸት ወንዝ አያሻግርም በፍፁም አትዋሹ፡፡ እውነተኛው ማንነታችሁን ብቻ ግለፁ፡፡ እስኪ እነዚህን ነገሮች በ CVዎቻችሁ ላይ አካቷቸው ጥሩ ነገር እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

Additional Tips:

COMMON INTERVIEW QUESTIONS

1. Tell us about yourself?

The interviewer is not interested in hearing stories; they simply expect  to know your academic and professional, achievements, your name and the institution or hotel you currently work for. Take a minutes to introduce yourself, and state your recent academic qualification and your relevant experience (if any).

2. Why do you think you are the best candidate?

The recruiter expects you to tell them about your professional achievements and the unique skills you possess that will add value to the organization. If you are a Customer Care graduate then you should tell them that you are a good listener and patient; these are the qualities the employer is looking for.

3. What are your weaknesses?

The question is not simple as it looks;  Most candidates go blank when they face this kind of question.

Take your time in explaining why you can’t leave the office before you complete a task.

You can also inform them how you are quick to trust a person, which in most cases makes you a victim.

4. Where do you see yourself in five years?

The employer wants to know whether, you are ambitious or you’re the kind of a person who secures a job and then you forget about yourself.

Answer the question by stating how you intend to further your studies and grow professionally as you strive to meet your employer’s goals. (It is important to tie your goals to your employer’s goals because no employer would be willing to hire and invest in a rookie who will leave their organization in a year or less after they have invested in training the individual)

5. How do friends describe you?

The question is testing your personal attributes, when answering it ensure that you don’t over exaggerate.

Take the shortest time possible to state the best attribute you possess that you believe will add value to the institution.

6. What do you know about this company?

Before you enter the interview room, ensure that you go through the company websit.

Good luck!

Stay in touches and follows us on our social media platforms to get the latest jobs opportunities.

Join our telegram channel

https://www.t.me/Ethiojob1Vacancy

COMMON JOB INTERVIEW QUESTIONS – በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ወደ 30 የሚደርሱ ጥያቄዎችንና ልትሰጡ የሚገባቸው ምላሾች
Spread the love
Scroll to top

You cannot copy content of this page